የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በትግራይ
በትግራይ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በዛሬው ዕለት መስጠት መጀመሩን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮ ሃላፊው ኪሮስ ጉዕሽን (ዶ/ር) በ1,189 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከ63 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና መቀመጣቸውን ገልጿል፡፡
ከእነዚህ ተፈታኞች ውስጥ 33,066 ወይም 52.3 በመቶ ሴቶች መሆናቸውም ተጠቁሟል፡፡
በሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሚጀመረው አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ላይ ለመቀመጥ 29,699 ተማሪዎች ተመዝግበው ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙም የክልሉ ትምህርት ቢሮ ጠቁሟል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
