የምርጫ ቦርድ ውሳኔ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም በፌዴራል እና ክልል መንግሥታዊ ተቋማት እንዲሁም የግል ተቋማት ሥራ ዝግ ሆኖ እንደሚውል አስታውቋል።
ቦርዱ ይሄን ያለው ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄደውን የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥን በተመለከተ በሰጠው ማብራሪያ ነው።
ቦርዱ ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
ቦርዱ ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በፌዴራል እና በክልሎች የሚገኙ ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ዝግ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
ቦርዱ የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪዎችም (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ የሚያከናውኑ መሆኑን ገልጾ የመተባበር ግዴታው የእነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አያስገድድም ብሏል።
የትራንስፖርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም፤ ዜጎች ድምፅ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችን እና ዕቅዶችን እንዳይይዙ እና እንቅስቃሴያቸውን ድምፅ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ ቦርዱ መክሯል።መረጃው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
