EthiopiaNews

የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ መስተጓጎል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲሱ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ሳቢያ የተወሰኑ ደንበኞቹ የአገልግሎት መስተጓጎል እንዳጋጠማቸው አስታወቀ።

ባንኩ ባወጣው መግለጫ ከአዲሱ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ጋር በተያያዘ የተወሰኑ ደንበኞቹ ላጋጠማቸው የአገልግሎት መስተጓጎል ይቅርታ ጠይቆ ችግሩን በአፋጣኝ ለመፍታት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን እና ችግሩ እንደተፈታም ለደንበኞቹ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

ባንኩ ከተሻሻለው መተግበሪያ ጋር በተገናኘ ችግር ያጋጠማቸው ደንበኞቹ ከታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ በመግባት፤ ወደ 951 ነፃ የደንበኞች የጥሪ ማዕከል በመደወል ወይም በባንኩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በመግባት ድጋፍ ማግኘት እንደሚችሉ አሳውቋል።
https://chat.whatsapp.com/BFR1h7SrAti091qznFEP4u

ባንኩ የተሻሻለውን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ በርካታ ደንበኞቹ እየተጠቀሙበት ነው ብሏል።

መረጃው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv