InternationalNews

የነዳጅ ዋጋ ዳግም ማሻቀብ

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ ከባድ ጥቃት እንደሚፈጸም መግለጻቸውን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ዳግም ማሻቀቡ ተሰምቷል።

ፕሬዝዳንቱ በቴሌቪዥን በቀጥታ ለሀገራቸው ሕዝብ በተሰራጨው ንግግራቸው ወቅት በቀጣይ ቀናት በኢራን ላይ ከባድ ጥቃት እንደሚፈጸም መናገራቸውን ተከትሎ ወደ 100 ዶላር ወርዶ የነበረው የአንድ በርሜል ነዳጅ ዋጋ ወደ 106 ዶላር መጨመሩ ነው የተነገረው፡፡

ለፕሬዝዳንቱ ንግግር ምላሽ የሰጡት የኢራን ጦር ቃል አቀባይ የኢራን ጦር የተፋፋመና ቀጠናውን የሚያሰፋ ከባድ ጥቃት ለመፈጸም ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡

የፕሬዝዳንት ትራምፕ ንግግር ምንም አዲስ ነገር ያልተሰማበት መሆኑን የሚጠቁመው የቢቢሲ ዘገባ ፕሬዝዳንቱ በዚህ ጦርነት በኢራን አገዛዝ የመቀየር ዓላማ ከመጀመሪያውም አልነበረኝም ማለታቸውን ጠቅሷል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews