EthiopiaNews

የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ኢትዮጵያ የኢራን ጦርነት ያደረሰውን ጫና ለመቋቋም እንድትችል ተጨማሪ የ200 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ሊፈቅድ መሆኑን አስታወቀ።

የገንዘብ ድርጅቱ የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ዜይን ዘይዳን ይሄን ያሉት ድርጅቱ በኢራን ጦርነት ለተጎዱ የአፍሪካ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

ዳይሬክተሩ የኢራን ጦርነት በተለይ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ጫና ማሳደሩን ተናግረዋል።

ኃላፊው አይኤም ኤፍ እንደ ቡርኪናፋሶ ፣ ጋምቢያ እና ሳኦ ቶሜ ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ጦርነቱ ያደረሰውን ጫና እንዲቋቋሙ ተጨማሪ ድጋፍ ለመልቀቅ ከስምምነት መድረሱን ገልፀዋል።

ኃላፊው አይ ኤም ኤፍ ለኢትዮጵያ የተራዘመ የብድር አቅርቦት መርሃ ግብር እየተገበረ መሆኑን አስታውሰው ሀገሪቱ 200 ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ ድጋፍ እንድታገኝ እየተሰራ ነው ብለዋል። ዘገባው የሮይተርስ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews