የአሜሪካ ድንበርና ጉምሩክ ጥበቃ በዳላስ አየር ማረፊያ 63 ኪሎ ግራም የሚመዝን የኢትዮጵያ ጫት መያዙን አስታወቀ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ድንበርና ጉምሩክ ጥበቃ በዳላስ አየር ማረፊያ 139 ፓውንድ ወይም 63 ኪሎ ግራም የሚመዝን የኢትዮጵያ ጫት መያዙን አስታወቀ፡፡
ባሳለፍነው ግንቦት 27 ቀን 2018ዓ.ም በቁጥጥር ስር የዋለው ይህ ጫት በአየር ጭነት ከኢትዮጵያ ተነስቶ ወደ ሳክራሜንቶ፣ ካሊፎርኒያ እየተጓዘ የነበረ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ባለሙያዎች ጫቱን ሊያገኙ የቻሉት ልዩ ልዩ የቅመማ ቅመም ዓይነቶች ተብሎ በተመዘገበ ጭነት ላይ ፍተሻ እያደረጉ በነበረበት ወቅት ሲሆን በተደረገው የእጽዋት ምርመራ ጫት መሆኑ ተነጋግጧል ነው የተባለው፡፡
በገበያ ላይ ወደ 17 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ያወጣል የተባለው ይህ ጫት ወዲያውኑ እንዲወገድ መደረጉንም የሀገሪቱ ድንበርና ጉምሩክ ጥበቃ ጠቅሷል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
