EthiopiaNews

አንጋፋው የኪነ ጥበብ ባለሙያ አዲስ ገሰሰ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል

አንጋፋው የኪነ ጥበብ ባለሙያ አዲስ ገሰሰ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል፡፡

የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃዎች ከዘመናዊ የሮክ ሙዚቃ ጋር በማቀናጀት ትልቅ ተወዳጅነትን ያተረፈው የጃኖ ባንድ መስራችና የቀድሞ ማናጀር አዲስ ገሰሰ ማረፉ ነው የተሰማው፡፡

ከጃኖ ባንድ በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ የቦብ ማርሌይ ልጆችን ጨምሮ በርካታ የሬጌ ሙዚቀኞች እንዲሁም በሀገር ውስጥ እንደ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) ያሉ ታዋቂ ድምፃውያንን ጋር በማናጀርነት የሰራ አንጋፋ የሙዚቃ ሰው ነው።

ኢትዮጵያውያን ሙዚቀኞች አለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኙ በማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረገው አዲስ ገሰሰ በኢትዮጵያ የሬጌ ሙዚቃ ፈር ቀዳጅ ድምጻዊ የሆነው እንዲሁም ሙዚቀኛና ፕሮዲውሰር አርቲስት ዘለቀ ገሰሰ እንዲሁም የታዋቂው የዳሎል ባንድ መስራችና የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች ሙሉጌታ ገሰሰ ወንድም ነው።

አዲስ ገሰሰ ከወንድሞቹ ጋር በመሆን የአፍሪካ እና የሬጌ ሙዚቃዎችን የሚያስተዋውቁ ትልልቅ ስራዎችን ከመስራት በተጨማሪ ከቦብ ማርሌ ልጅ ዚጊ ማርሌ እና ከወንድሞቹ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች በጎ ስራዎችን ሰርቷል፡፡

ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv