የአውሮፓ ህብረት መግለጫ
የአውሮፓ ህብረት በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ወቅታዊ ውጥረት ላይ ያለውን ከፍተኛ ስጋት ገለጸ።
ህብረቱ ባወጣው መግለጫ፣ በተለይም ህወሐት በትግራይ ክልል ትይዩ የክልል ምክር ቤት ለማቋቋምና የተናጠል የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ለማካሄድ የወሰዳቸው እርምጃዎች እ.ኤ.አ. በ2022 የተፈረመውን የፕሪቶሪያን የሰላም ስምምነት የሚጥሱ መሆናቸውን አስታውቋል።
የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በተጨባጭ መሬት ላይ ለማውረድ ሁሉም ወገኖች በአስቸኳይ ወደ ውይይት ጠረጴዛ እንዲመለሱ አሳስቧል።
በክልሉ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦባሳንጆ የሚመራውን የሽምግልና ጥረት ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍ የአውሮፓ ህብረት አረጋግጧል።