የኢቦላ ወረርሽኝ መስፋፋት
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኢቦላ ወረርሽኝ ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር 131 መድረሱ ተነገረ።
ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 513 መሻገሩን ያሳወቁት የኮንጎ ባለስልጣናት በሽታው በሀገሪቱ በፍጥነት እየተስፋፋ እንደሚገኝም ነው የገለጹት፡፡
የኮንጎ ጎረቤት ሀገር ዩጋንዳ ባለስልጣናት ደግሞ እስካሁን ሁለት ሰዎች በሽታው እንዳለባቸው መረጋገጡንና አንድ ሰው በበሽታው ሕይወቱ ማለፉን ጠቅሰዋል፡፡
የዓለም የጤና ድርጅት ቡንዲቡግዮ በተሰኘው ቫይረስ የሚመጣውን ይህንን በሽታ የዓለም የጤና ስጋት ሲል ማወጁ የሚታወስ ሲሆን በሽታው ወደ ሌሎች የቀጠናው ሀገራት እንዳይስፋፋም ስጋት ማጫሩ ነው የተነገረው፡፡ ዘገባው የሲ.ኤን.ኤን ነው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/
