የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 2.1 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘቱን አስታወቀ።
ባንኩ ይህንን የገለጸው 2025/26 የበጀት አመት የስራ አፈጻጸሙን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ።
ባንኩ በዘርፉ በሁለት አመት ውስጥ ከ5 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማግኘቱን ከዚህም የበጀት አመቱ ድርሻ 2 ነጥብ1 ቢሊየን ዶላር መሆኑን ገልጿል፡፡
ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተለያዩ ዘርፎች 648 ቢሊየን ብር ብድር መስጠቱንም አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበላሸ የብድር ምጣኔ 1.4 በመቶ ብቻ ነው ተብሏል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
