የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገቢ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ዓመት 8 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዶ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።
አየር መንገዱ የዛሬ ስምንት ዓመት 3 ቢሊየን ዶላር አመታዊ ገቢ እንደነበረው ጠቅሶ ባለፉት ስምንት አመታት ወደ 7 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ማደጉን ገልጿል።
በፈረንጆቹ 2040 አየር መንገዱን በዓለም ላይ ካሉ ቀዳሚ 20 የአቪዬሽን ግሩፖች ውስጥ አንዱ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን ገቢውንም ወደ 29 ቢሊየን ዶላር ለማሳደግ ማቀዱ ጠቁሟል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
