የኢትዮጵያ የቡና ምርት
ኢትዮጵያ በሚቀጥለው የአውሮፓውያኑ አመት ከአለም 4ተኛዋ ከፍተኛ ቡና አምራች አገር እንደምትሆን የአሜሪካ ግብርና ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
የአሜሪካ ግብርና ዲፓርትመንት ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያ በሚቀጥለው አመት ከ700 ሚሊዮን ኪሎ በላይ የቡና ምርት በማምረት ከአለም 4ተኛዋ ትልቋ የቡና አምራች ሀገር ልትሆን እንደምትችል ነው ግምቱን ያስቀመጠው፡፡
የኢትዮጵያ የቡና ምርት ባለፉት 3 ተከታታይ አመታት እያደገ መምጣቱንና አሁንም ብራዚል፣ ቬትናምና ኮሎምቢያ ቀዳሚ ቡና አምራች ሀገራት መሆናቸውንም ሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
