EthiopiaNews

የመገኛኛ ብዙሃን በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ

7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለመዘገብ 1 ሺህ 814 የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች መመዝገባቸውን ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ የሚዲያ ተቋማት ቁጥር ከ122 ወደ 310 ማደጉ፣ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመራቸው እንዲሁም የመረጃ ተደራሽነት በ60 ቋንቋዎች መሆኑ ለዴሞክራሲያዊ ውይይት ሰፊ እድል መፍጠሩንም ነው ቦርዱ የጠቆመው፡፡

የዘንድሮው ምርጫ ይበልጥ አካታችና አሳታፊ እንዲሆን ቦርዱ 55 ድርጅቶችን ለታዛቢነት ማሰማራቱን የተጠቀሰ ሲሆን ከ220 ሺህ በላይ የፓርቲ ወኪሎችንም በማገዝ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews