የኤምባሲው ጥሪ
በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጲያ ኤምባሲ በሀገሪቱ ግድያ እየፈፀሙ ያሉ አካላት ላይ ምርመራ በማካሄድ እርምጃ እንዲወሰድ ለፕሪቶሪያ መንግስት ጥሪ አቀረበ።
ኤምባሲው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ከሰሞኑ በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ በተፈፀመው ግድያ ማዘኑን ገልጿል።
ኤምባሲው በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ጊዜያት አካላዊ ፣ ቁሳዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑን ገልፆ ችግሩ ትኩረት እንዲሰጠው ለደቡብ አፍሪካ መንግሥት ማሳሰቡን አስታውሷል።
ኤምባሲው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደቡብ አፍሪካ እያደገ የመጣውን እና በሰፊው የውጭ ዜጐች በተለይም የጥቁር ስደተኛ ጠል እንቅስቃሴ እየተበራከተ መምጣቱን ገልፆ የኘሪቶሪያ መንግስት በሀገሪቱ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርግ መጠየቁን አስታውቋል።
ኤምባሲው በቀጣይም ተጨማሪ የዜጐች ህይወት እንዳይጠፋ ችግሮች በሚታዩባቸው አካባቢዎች ልዩ ጥበቃ እንዲደረግ እና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር የውይይት መድረክ እንዲዘጋጅ በደብዳቤ መጠየቁን ገልጿል።
ኤምባሲው አሁን ያጋጠመው ችግር እስኪፈታ ድረስ በደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያን እራሳቸውን እና ንብረታቸውን እንዲጠብቁ ፣ ከአካባቢው አስተዳደር እና የፀጥታ አካላት ጋር እንዲሰሩ እና ችግሮች ሲያጋጥማቸው ለኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲያሳውቁ ጥሪ አቅርቧል።
ከቀናት በፊት በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ሦስት ኢትዮጵያዊያን በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን የሀገሪቱ መንግስት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
መረጃው በደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው የኢትዮጲያ ኤምባሲ የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
