የካናዳ ስራ ስምሪት
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል እና ከካናዳ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ዜጎችን አሰልጥኖ ወደ ካናዳ ለመላክ ያደረገውን ስምምነት አስመልክቶ ዜጎች አጭበርባሪዎች ከሚያሰራጯቸው ሃሰተኛ መረጃዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል፡፡
ስምምነቱን አንዳንድ ሕገ-ወጥ አካላት ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የተፈበረኩና አሳሳች ምስሎችንና በዲዮዎችን ማሰራጨት ምዝገባ ተጀምሯል የሚሉ ሀሰተኛ መረጃዎችን በመልቀቅ ማህበረሰቡን ማደናገር ላይ እንደሚገኙ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል፡፡
ሆኖም እነዚህ ማስታወቂያዎች ሙሉ በሙሉ የማጭበርበር ተግባራት መሆናቸውን ያሳወቀው ተቋሙ ዜጎች ለኢኮኖሚያዊ ብዝበዛ እንዳይጋለጡና ከዲጂታል ማጭበርበርና ከሀሰተኛ መረጃዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በአሁኑ ወቅት ለካናዳ የሥራ ስምሪት ምንም አይነት ይፋዊ ምዝገባ እንዳልተጀመረ የገለጸ ሲሆን በግል ስልክ ቁጥሮች የሚደረጉ ጥሪዎችም ሆኑ የሚላኩ አጫጭር መልዕክቶች ሚኒስቴሩን አይወክሉም ብሏል፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
