የክልሉ የወርቅ ምርት
የጋምቤላ ክልል ማዕድን ቢሮ 5 ሺህ 535 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማስገባቱን አስታወቀ።
ቢሮው ይሄን ያለው የ2018 በጀት ዓመት 9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ነው።
በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በዘርፉ የታየው አፈፃፀም ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነፃጸር ከአንድ ሺህ 278 ኪሎ ግራም በላይ የወርቅ ምርት ብልጫ ያለው መሆኑ ተገልጿል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ የወርቅ ማዕድን ሀብት እንደ ሀገር ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች አንዱ ነው መሆኑን ጠቅሰው በክልሉ ያለውን የወርቅ ማዕድን ሀብት ልማት በማዘመን ጥቅም ላይ ለማዋል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሯ በቀጣይ ሶስት ወራትም 1 ሺህ 500 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
