የክትባት ዘመቻ
በኢትዮጵያ በግጭት በተጎዱና ራቅ ባሉ አካባቢዎች የተቀናጀ የክትባትና የጤና ምርመራ ዘመቻ ተደራሽ መሆን መጀመሩን የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ማዕከል አስታወቀ።
በሃገሪቱ በግጭት በተጎዱና ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች፣ የኮቪድ-19 ክትባትንና ተላላፊ ያልሆኑ ሽታዎች ምርመራ የሚያቀርብ የተቀናጀ የጤና አገልግሎት ማግኘት መጀመራቸው ነው የተገለጸው።
በማስተርካርድ ፋውንዴሽን እና በአፍሪካ ሲዲሲ በተገኘ ድጋፍ በጤና ሚኒስቴርና በአምሬፍ ሄልዝ አፍሪካ የሚተገበረው ይህ የሕይወት አድንና የኑሮ ማሻሻል መርሃ ግብር፣ አረጋውያንንና ሥር የሰደደ ሕመም ያለባቸውን ወገኖች ጨምሮ በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለመድረስ ትኩረት ያደረገ ነው ተብሏል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
