EthiopiaNews

የኮንትሮባንድ ዕቃዎች

የገቢዎች ሚኒስቴር ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታወቀ።

የጉምሩክ ኮሚሽን ከሚያዚያ 11 እስከ ሚያዚያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረገው ክትትል በጅግጅጋ ፣ በአዲስ አበባ ኤርፖርት እና በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች 386.2 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 14.5 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 400.7 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተይዘዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል አዳዲስ እና ልባሽ ጨርቆች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግብርና ምርቶች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ የተለያዩ ማዕድናት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 26 ተጠርጣሪዎች እና 10 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

መረጃው ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv