EthiopiaNews

የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገነባው የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ የፊታችን ሰኔ ወር መጨረሻ እንደሚመረቅ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይሄን ያሉት “የሉዓላዊነት ልብ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ክፍል ሁለት የበተለይ ቃለመጠይቅ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጲያ እስካሁን ጥሬ ወርቅን ወደ ውጭ በመላክ ላይ ብቻ ተወስና መቆየቷን አስታውሰው አሁን እየተገነባ ያለው ፋብሪካ በዘርፉ ያለውን የእሴት መጨመር ችግር እንደሚቀርፈው ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፊታችን ሰኔ ወር መጨረሻ የሚመረቀው የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካው በሀገር ውስጥ እና በአካባቢው የሚመረተውን ወርቅ እሴት ታክሎበት በተሻለ ዋጋ ለገበያ ለማቅረብ ከፍተኛ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews