EthiopiaNews

የዕዳ ሽግሽግ ድርድር

ከአበዳሪ ተቋማትና ከአጋር አገራት ጋር ሲደረግ የቆየው የዕዳ ሽግሽግ ድርድር በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን እና በቀጣይ ጊዜያት መንግስት ወደ ዕዳ ክፍያ እንደሚገባ የገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ9 ወራት አፈጻጸሙን በተመለከተ ባካሄደው መድረክ በቀጣይ ቀሪ የሥራ ጊዜያት መንግስት ወደ ዕዳ ክፍያ እንደሚገባ ጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙ አማካኝነት በውጭ ምንዛሪ ክምችት፣ በኤክስፖርት፣ በውስጥ ገቢ አሰባሰብና በመሳሰሉት ረገድ ውጤቶች መመዝገባቸውንም ገልጿል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv