EthiopiaNews

የዘንድሮ 12ኛ ክፍል ፈተና 

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበትን ቀን ይፋ አደረገ።

 

አገልግሎቱ ባወጣው መግለጫ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 24 እስከ ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ ገልጿል።

 

አገልግሎቱ የሪሚዲያል ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 17 እስከ 20 እና የቅደመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ 12  ይሰጣል ብሏል፡፡

 

የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከሐምሌ 29 እና 30 ቀን 2018 ዓ.ም ሲሰጥ  የመሰረታዊ የንባብና የስሌት ክህሎት ምዘና ፈተና ደግሞ ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ውስጥ ይሰጣል ተብሏል፡፡

 

መረጃው ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተገኘ ነው።

 

#EBS

#EBSTVNEWS

#EBSTVSPORT

#_7696_WN

https://t.me/ebstvnews

www.ebstv.tv