Ethiopia

የዳንጎቴ ኩባንያ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት

🔸የዳንጎቴ ኩባንያ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በጋራ በጎዴ እያስገነባው ላለው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ መድቦት የነበረውን የ2.5 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ወደ 4 ቢሊየን ዶላር ማሳደጉን አስታወቀ።

🔸የዳንጎቴ ግሩኘ ፕሬዚዳንት አሊኮ ዳንጎቴ ይሄን ያሉት ትናንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በመሆን በጎዴ እየተገነባ የሚገኘውን የዩሪያ ማዳበሪያ ግንባታ አፈፀፀም ከገመገሙ በኋላ ነው።

🔸ናይጄሪያዊው ባለፀጋ አሊኮ ዳንጎቴ አሁን ያሳደግነው ተጨማሪ ኢንቨስትመንት በጎዴ 110 ኪሎ የሚረዝም የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ ቱቦ መስመር ዝርጋታ ፣120 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጭ የኃይል ማመንጫ እና ሌሎች የፓኬጂንግ ፋብሪካ ግንባታዎችን እውን የሚያደርግ ነው ብለዋል።

🔸ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በጎዴ እየተገነባ የሚገኘው በዓመት 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ የማምረት ዐቅም ያለው ፋብሪካ ግንባታ በተያዘለት ዕቅድ መሠረት እየተከናወነ እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል።

👉መረጃው ከዳንጎቴ ግሩፕ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN