የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮ ለመክፈት
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችን ለመክፈት ፍላጎቱ እና ዝግጁነቱ ላላቸው የሥራ ፈቃድ ማመልከቻዎችን መቀበል መጀመሩን ይፋ አድርጓል ።
የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸው በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚኖሩ እንዲሁም የሌላ ሀገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የውጭ ምንዛሪ ቢሮ መስፈርቶችን አሟልተው ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ሲያገኙ መክፈት እንደሚችሉም ተነግሯል፡፡
በዚህ የሥራ መስክ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ዝርዝር መረጃ ከባንኩ ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ መመልከት ትችላላችሁ።