EthiopiaNews

የጣሊያን ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ያለው የጣሊያን ኢንቨስትመንት ከ720 ሚሊዮን ዩሮ በላይ መድረሱ ተገልጿል።

ይህንን በሁለቱ ሀገራት መካከል እያደገ የመጣውን የኢኮኖሚ ትብብር በይበልጥ የሚደግፍ “ቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ” የተሰኘ ኤግዚቢሽን ከመጪው ሚያዝያ 15 እስከ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል እንደሚካሄድም ተጠቁሟል፡፡

በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ ከ20 በላይ የጣሊያን ኩባንያዎች ይሳተፋሉ ነው የተባለው።

ጣሊያን ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በዘላቂ ልማትና በኢኮኖሚ አጋርነት ላይ ለማተኮር ይፋ ባደረገችው ማቴይ ፕላን የተሰኘ ስትራቴጂ ውስጥ በተካተተችው ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ኤግዚቢሽን መካሄዱ የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት እንደሚያጠናክርም ታምኖበታል፡፡

የጣሊያን የንግድ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ክላውዲዮ ፓስኳሉቺ ይህ ኤግዚቢሽን ለተሳትፎ የሚደረግ ሳይሆን በአፍሪካ ተስፋ ሰጪ ከሆኑ ገበያዎች በአንዱ ያለንን ቦታ ለማጠናከርም ያለመ ነው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ወደ 150 የሚጠጉ የጣሊያን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በንግድ እና በኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙም የጣሊያን መንግስት መረጃ ያመላክታል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/