EthiopiaNews

የፌዴራል መንግሥት የ2019 በጀት 2.34 ትሪሊዮን ብር ሆኖ ፀድቋል፡፡

የኢፌዴሪ የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባካሄደው 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባው 2 ነጥብ 34 ትሪሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን የፌዴራል መንግስቱን በጀት አጽድቋል።

የ2018 በጀት ዓመት የፀደቀው በጀት 1.93 ትሪሊዮን ብር የነበረ ሲሆን፣ በምክር ቤቱ የጸደቀው አዲሱ የ2019 ዓ.ም አጠቃላይ በጀት ደግሞ ካለፈው በጀት አመት ከ400 ቢሊዮን ብር በላይ ጭማሬ ያለው ነው፡፡

የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ይህ በጀት የአገሪቱን የፋይናንስ አቅምና የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲን ያገናዘበ መሆኑን በውሳኔ ሃሳቡ አመልክቷል።

ከተያዘው አጠቃላይ ወጪ ውስጥ 1.49 ትሪሊየን ብር ከታክስ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱ በምክር ቤቱ ተገልጿል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv