EthiopiaNews

የፓትርያርኩ ማሳሰቢያ

🔸ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅና ሰላምን የማስፈን አደራ የተጣለባቸው የጸጥታ አካላት በቤተ ክርስቲያንና በምእመናን ላይ የሚደርሰውን የጥቃት ሰንሰለት እንዲያስቆሙ ጥሪ አቀረቡ።

🔸ፓትርያርኩ ይህንን ጥሪ ያቀረቡት  በአርሲ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያንና በምእመናኑ  ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስመልከት መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በተለይ በአሰኮ፣ በሽርካ፣ በሆንቆሎ፣ በዋቤና በሙኔሳ ወረዳዎች  ጥቃት መድረሱን ገልጸዋል።

🔸የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ለዝግጅት ክፍላችን የላከው መግለጫ እንደሚያሳየው  በዚሁ ጥቃት  መቶ ዓመታትን ያስቆጠረው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን እንዲሁም የካራ ኩፍቴና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን መዘረፉ ተገልጿል።

🔸እንዲሁም በርካታ ምእመናን በግፍ መገደላቸውንና በመቶዎች የሚቆጠሩ ምእመናንም  ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው ተጠቁሟል።

🔸አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ በዚሁም መልእክታቸው የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅና ሰላምን የማስፈን አደራ የተጣለባቸው  የጸጥታ አካላት በቤተ ክርስቲያንና በምእመናን ላይ የሚደርሰውን የጥቃት ሰንሰለት  እንዲያስቆሙ እንዲሁም ወንጀለኞችንም ለሕግ እንዲያቀርቡ  ጥሪ አቅርበዋል።

🔸ፓትርያርኩ ጨምረውም በየአካባቢው የሚገኙ ምእመናንና መላው ኢትዮጵያውያን የተፈናቀሉ ወገኖችን እንዲደግፉ ጠይቀዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews