EthiopiaNews

የፕሬስ ነጻነት በኢትዮጵያ

ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት አር ኤስ ኤፍ ባወጣው የፕሬስ ነጻነት ሁኔታ በሚመዘንበት የ2026 ዓለም አቀፍ ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ ከ180 ሀገራት 148ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ገለጸ፡፡

ድርጅቱ ባሳለፍነው የአውሮፓውያኑ አመት ባወጣው ዝርዝር ኢትዮጵያ 145ኛ ደረጃ ላይ የነበረች ሲሆን በአሁኑ ወቅት ደግሞ ወደ 148ኛ ዝቅ ማለቷን ጠቅሷል፡፡

በዚሁ ዝርዝር ውስጥ በ1ኛ ደረጃ የተቀመጠችው ኖርዎይ ስትሆን የመጨረሻውን ማለትም 180ኛ ደረጃውን የያዘችው ደግሞ ኤርትራ መሆኗ የተጠቀሰ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የአለም ሀገራት ለፕሬስ ነፃነት አስቸጋሪ ወይም በጣም አሳሳቢ ምድቦች ውስጥ የሚወድቁ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv