ፈልጉልኝ መተግበሪያ
የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አካል የሆነና አሠሪና ሠራተኞችን በቀላሉ ማገናኘት የሚያስችል ‘ፈልጉልኝ’ የተሰኘ ሀገራዊ ዲጂታል መተግበሪያ በይፋ አስመርቆ ወደ ሥራ ማስገባቱን አስታወቀ።
የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ወደ ሥራ የገባው ይህ ዲጂታል መተግበሪያ በሥራ ገበያው ውስጥ ያለውን የመረጃ ክፍተት በመቅረፍ ሥራ ፈላጊ ዜጎችንና አሠሪዎችን ካሉበት ሆነው በቀጥታ የሚያገናኝ ዘመናዊ የሥራ ሥነ-ምህዳር ነው ብለዋል።
ሚነስትሯ መተግበሪያው መደበኛ ያልሆነውን የሥራ ዘርፍ ወደ መደበኛ የኢኮኖሚ ሥርዓት የሚያሸጋግር መሆኑን ገልፀው በማስረጃ ላይ የተመሠረተ የፖሊሲ ቀረጻን በማገዝ እና አስተማማኝ የመረጃ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ አኳያም ሚናው የላቀ ነው ብለዋል።
በቴክኖሎጂ አማካኝነት የሥራ ገበያውን ትክክለኛ ፍላጎት በማሳየት፣ የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የሥራ ገበያው የሚፈልገውን ብቁ የሰው ኃይል እንዲያፈሩ መተግበሪያው ስልታዊ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል።
መረጃው ከስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገፅ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
