EthiopiaNews

የኢቦላ ወረርሽኝ

የጤና ሚኒስቴር እስከዛሬ ድረስ በኢትዮጵያ ምንም አይነት በኢቦላ ቫይረስ የተጠረጠረ ወይም የታመመ ሰው እንዳልተገኘ አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው ከኢቦላ ቫይረስ በሽታ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ እየተደረጉ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ላይ ነው።

ሚኒስቴሩ ኢትዮጵያ በሽታው ከተገኘባቸው አገራት ጋር ቀጥተኛ የድንበር ግንኙነት እንደሌላት ገልጾ ይሁን እንጂ የበሽታውን አደገኛነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ጥብቅ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወነ መሆኑን አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ እያካሄደ ካላቸው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ውስጥ በሁሉም አለም አቀፍ የየብስ መግቢያ እና መውጫ ኬላዎች የመለየት እና የቅኝት ስራዎችን የማጠናከር ፣በአለም አቀፍ አየር ማረፊያዎች ክትትል ማድረግ ፣
እና የጤና ተቋማት ዝግጁ የማድረግ ይገኙበታል።

የአለም የጤና ድርጅት በዴሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ እስካሁን 220 ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ ብሏል።

መረጃው ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv