InternationalNews

የአሜሪካና ኢራን ስምምነት

🔸የአሜሪካው ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የአሜሪካና ኢራን ጠንካራ የተባለ ስምምነት ዛሬ ይፋ ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገለፁ።

🔸በሕንድ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አሸማጋዮች ጦርነቱን መደምደም በሚያስችል የሰላም ዕቅድ ላይ እየሰሩ መሆኑን ገልጸው በዛሬው ዕለትም የመጨረሻው ስምምነት ይፋ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

🔸ዛሬ ይፋ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት በ60 ቀናት የሚያራዝም ከመሆኑም ባሻገር የሆርሙዝ ሰርጥ እንዲከፈትና በኢራን የኒውክለር ፕሮግራም ዙሪያ ቀጣይ ድርድሮች እንዲኖሩር ያደርጋል ተብሏል፡፡

🔸ይህ መረጃ መሰማቱን ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ በተወሰነ ደረጃ ቅናሽ ማሳየቱ ሲነገር የእስያ የአክስዮን ገበያ ዋጋም ማንሰራራቱን ጠቅሶ የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews