InternationalNews

የኢቦላ መስፋፋት

🔸በዲሞክራቲክ ኮንጐ በተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 900 ደረሰ።

🔸አርቲ የዓለም ጤና ድርጅትን ጥቅሶ እንደዘገበው ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ 101 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል።

🔸የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል ቴድሮስ አድሃኖም በኤክስ ገፃቸው እንዳሉት በአገሪቱ ያለው ሁከትና መፈናቀል የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር አስቸጋሪ አድርጐታል።

🔸በአገሪቱ 5 ሚሊዮን ዜጎች በጦርነት አካባቢ ይኖራሉ፤ ከእያንዳንዳቸው 4 ሰዎች አንዱ እርዳታ ይፈልጋል፤ ከ5 ሰዎች አንዱ ደግሞ ከመኖሪያው ተፈናቅሎ የሚገኝ በመሆኑ ይሄ ሁኔታ ለመከላከል ጥረቱ ፈተና ይጋርጣል ብለዋል።

🔸በኢቦላ የሞቱ ሰዎች ዘመዶች የሟች አስክሬን ይሰጠን በሚል የህክምና ተቋማት ላይ ጥቃት እስከመሰንዘር መድረሳቸው ሰሞኑን ሲዘገብ ቆይቷል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews