EthiopiaNews

‎የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

🔸የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ1447ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል ወቅት የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡

🔸በተለይ ደግሞ በበዓላት ሰሞን ደንበኞች ቀኑን በድምቀት ለማክበር ከወትሮው የተለየ የኃይል አጠቃቀም እንደሚኖራቸው የገለጸው አገልግሎቱ የሚፈጠረውን ከፍተኛ ጫና ለመቀነስ በልዩ ትኩረት የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱንም ጠቅሷል፡፡

🔸ከበዓሉ አስቀድሞ ከተሰሩ ስራዎች መካከል የመካከለኛና የዝቅተኛ ማሰራጫ መስመሮችን የመፈተሸ፣ የረገቡ የኤሌክትሪክ ገመዶችን የመወጠር፣ የእንጨት ምሰሶዎችን በኮንክሪት የመቀየር፣ የኃይል ጫና ያለባቸውን ትራንስፎርመሮችን ዓቅም የማሳደግ ስራዎች እንደሚገኙበትም ተገልጿል፡፡

🔸በዚህም አገልግሎቱ የሚያስተዳድረው ነባር መሰረተ ልማት ላይ ሙሉ ለሙሉ የቅድመ መከላከል ፍተሻ ማካሄዱን የጠቀሰ ሲሆን ለኃይል መቆራረጥ መንስኤ ከሆኑ ግኝቶች መካከል በዋናው ኔትዎርክ 80 በመቶ እንዲሁም በትራንስፎርመር 70 በመቶ የሚሆኑትን መቅረፍ ተችሏል ነው ያለው፡፡

🔸የኃይል መቆራረጥ ለመቀነስ፤ ሲከሰትም አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ግብረ-ሃይል መዋቀሩን ያስታወቀው አገልግሎቱ በበዓሉ ዕለት በተመረጡ ማዕከላት የካርድ መሙላት አገልግሎት እንደሚሰጥ የጠቀሰ ሲሆን ሆኖም  የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ተጠቃሚ ደንበኞች የገዙትን የኃይል መጠን ማለቅና አለማለቁን በማረጋገጥ በዓሉ ከመድረሱ በፊት አስቀድመው እንዲሞሉም ጥሪውን አቅርቧል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv