EthiopiaNews

ምርጫ በወታደራዊና ተፈናቃይ ካምፖች

ተፈናቃዮችና በወታደራዊ ካምፖች የሚገኙ ዜጎች ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ለሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምጻቸውን እየሰጡ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና በወታደራዊ ካምፖች ልዩ ጣቢያዎችን በማቋቋም የካምፑ ነዋሪዎችን በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ እንዲሳተፉ በመራጭነት መመዝገቡን ያስታወሰው ቦርዱ በዛሬው እለትም የድምፅ አሰጣጡ እየተካሄደ መሆኑን አሳውቋል።

ባለፈው ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ መስጠት ሂደት መካሄዱ የሚታወቅ ሲሆን ቦርዱ በአሁን ወቅት ከምርጫ ክልል ጽህፈት ቤት ወደ ቦርዱ ማዕከል በመምጣት ላይ ያሉ ውጤቶችን የማረጋገጥ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

በተመሳሳይ የኦዲት ግኝት ያለባቸውን ውጤቶችን ደግሞ የመመርመር እንዲሁም የተረጋገጡ ውጤቶችን ወደ መረጃ ቋት የማስገባት ስራ እየተሰራ ነው ብሏል፡፡

በቀጣይም በተጠቀሰው ሂደት ያለፉ ውጤቶች ለቦርድ ውሣኔ በማቅረብ እና በማፀደቅ በሕጉ መሠረት ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews