InternationalLatestNews

በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተው ድርቅ

በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተው ድርቅ እስካሁን 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑ የቁም እንስሳዎችን እንደገደለና በርካቶችንም ለምግብ እጥረት እንዳጋለጠ ፋኦ አስታውቅዋል፡፡የአለም የምግብ ፕሮግራም በቀጠናው የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ 1.5 ሚሊዮን የቁም እንስሳዎች መሞታቸውንና የተጋረጠውን የድርቅ አደጋ ለመቀልበስ ያለው ተስፋ የተመናመነ መሆኑን አስታውል፡፡ድርቁን ተከትሎ የአልሚ ምግብ አቅርቦቱ በሶማሌያ ከዚህ በፊት ከነበሩት አመታት ወደ 58 በመቶ ዝቅ ማለቱን ገልጾ በኬንያም እንዲሁ የቀጠለውን ድርቅ ተከትሎ የአልሚ ምግብ አቅርቦት ወደ 70 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተመልክተዋል፡፡በቀጣዩ ወር በቀጠናው የምግብ ድጋፍ ለማቅረብ 130 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የገለጹ ሲሆን ድርቁ የሚቀጥል ከሆነ ግን መጪው ጊዜ ለቀጠናው አስከፊ ነው የሚሆነው ሲል ፋኦ ስጋቱን ገልጽዋል፡፡የአለም የምግብ ፕሮግራም መረጃ እንደሚያሳየው በቀጠናው የተከሰተው ድርቅ 13 ሚሊዮን ዜጎችን ለረሀብ አደጋ የጣለ ሲሆን ይህም በኢትዮጵያ ከ37 አመታት በፊት ከተከሰው የድርቅ አደጋ ጋር ሊስተካከል የሚችል ነው ተብሏል በቀጣዩ ስድስት ወራትም 4.6 ሚሊዮን የሚደርሱ ዜጎች አፋጣኝ የዕለት ደራሽ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል፡፡ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Telegram: https://t.me/ebstvworldwide

Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision