EthiopiaLatestNews

የአስቸኳይ ጊዜው አዋጅ መነሳት

ለስድስት ወራት እንዲቆይ በሃገሪቱ ተጥሎ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጊዜው ሳይደርስ ዛሬ መነሳቱ ታውቋል።ምክር ቤቱ ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 15 ቀን 2014 ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ አዋጁን ማውጣት የግድ አስፈላጊ እንዲሆን አድርጎ የነበረው ሁኔታ ጉልህ በሆነ መልኩ የተቀየረ መሆኑንና ስጋቱን በመደበኛ የህግ ማስከበር ሂደት መከላከል የሚቻልበት ሁኔታ ላይ በመደረሱ አዋጁ እንደነሳ ተጠይቋል ተብሏል፡፡ ምክርቤቱ የቀረበለትን አጀንዳ ውይይት ካደረገበት በኋላም በ63 ተቃውሞ በ21 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወስኗል።ይህን ውሳኔ ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ያላጠናቀቃቸው ጅምር ስራዎች ካሉ ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት ከዛሬ ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንዲያደርግ ተወስኗል፡፡ያ

ሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Telegram: https://t.me/ebstvworldwide

Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision