EthiopiaLatestNewsSports

የኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ አለም አቀፍ ውደሳዎች

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ የትላንትናውን ጨዋታ ተከትሎ አለም አቀፍ ውደሳዎች እየዘነቡለት ይገኛል፡፡ በግማሽ ፍጻሜ ሴኔጋል ቡርኪናፋሶን 3ለ1 በመርታት ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ለፍጻሜ ያለፈችበትን ጨዋታ በሚገባ የመራው አልቢትሩ በተለይ ለታራንጋ አንበሶቹ የተሰጡትን ሁለት የፍጹም ቅጣት ምቶች በቫር ከተመለከተ በኋላ የሻረበት መንገድ የብዙዎችን ቀልብ የሳበ ሆኗል፡፡ይህንን ተከትሎም በአለም ዙሪያ ያሉ የእግር ኳስ አፍቃሪያን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች አድናቆታቸውን እያዥጎደጎዱለት ይገኛል፡፡ ከነዚህም መካከል በአለም አቀፍ ከሚገኙ ደረጃ አንድ ዳኞች መካከል አንዱ ነው፤የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዳኞች ከሱ ሊማሩ ይገባል፤የውድድሩ ምርጥ ዳኛ እሱ ነው እና የፍጻሜውን ጨዋታ ሊመራ ይገባል የሚሉት በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ዴሊሜልም እነዚህን እና ሌሎች ስለ ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ የተሰጡ አድናቆቶችን በሰፊው በገጹ ይዞ ወጥቷል፡፡የካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታው ሊጠናቀቅ 5 ደቂቃ እየቀረው ጨዋታው መጠናቀቁን ያበሰሩ እና ተጫዋች እስከ መማታት የደረሱ ዳኛን እንዳስመለከተን እንዲሁም 13 የቀይ ካርዶች እንደተመዘዙበት የሚታወቅ ነው፡፡

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Telegram: https://t.me/ebstvworldwide

Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision

#ኢቢኤስ#EBS