በሴቶች ጥቃት እና ሰላም አምጪነት ዙሪያ ዉይይት ተደረገ

የሰላም ሚኒስቴር ከአይ ኤስ ኤስ/Institute for Security Studies/ ጋር በመተባበር የሴቶችን ጥቃት እና የሰላም አስተዋጾ ላይ ተወያዩ፡፡

በሚኒስቴር መ/ቤቱ የብሔራዊ መግባባትና ማኅበራዊ ሃብት ግንባታ ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ሚናስ ፍስሓ በፓለቲካ አለመግባባት ምክንያት በሚፈጠሩ ግጭቶች ሴቶች የመጀመሪያው ተጠቂ እንደሚሆኑ ገለጸዋል። ግጭቶችን ለመፍታትና ሰላምን ለማጎልበት ሴቶች ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳላቸዉም ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ ኢትዮጵያ በገጠማት ችግር የሴቶች ጥቃት እንዲሁም በሰላም ግንባታ እረገድ ሚያደርጉትን ከፍተኛ ጥረት አስመልክቶ ሰፊ ምክክር ተደርጓል።