በባቲና በከሚሴ ግንባር የህወሓት አመራሮች መደምሰሳቸው ተገለፀ::

በመንግሥት የፀጥታ ኃይል በባቲና በከሚሴ ግንባር በተወሰደ የተቀናጀ እርምጃ በሽብር የተፈረጀው የህወሓት ቡድን ጦር ሲመሩ የነበሩ አመራሮች መደምሰሳቸው ተገለፀ::የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ማምሻውን ለመንግስት ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ ባለፉት 2 ቀናት በባቲ ግንባር በተደረገ ልዩ ኦፕሬሽን 6 የአርሚ እና የኮር ከፍተኛ አመራሮች ውስጥእነዚህም በፌደራል መንግሥት በሀገር ክህደት ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ ጀኔራሎችና ኮሎኔሎች መሆናቸውን አመልክተዋል። በዚሁ በባቲ ግንባር በዛሬው ዕለት በተደረገው ከፍተኛ የማጥቃት እርምጃ ቀደም ሲል ከነበሩ ጥቃቶች ተርፎ ለዳግም ማጥቃት ሲዘጋጅ የነበረው የጠላት ኃይል የተደመሰሰ ሲሆን፤ እግሬ አውጪኝ ብሎ ወደ ኋላ የፈረጠጠውን ቡድን የወገን ጦር እያጸዳ ወደ ፊት እየገሰገሰ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡በሌሎችም ግንባሮች ጠላት በከፍተኛ ሁኔታ እየተመታ ሲሆን፣ የወገንን ክንድ መቋቋም አቅቶት በተናጠልና በቡድን ወደ ኋላ የሚሸሸው ሃይል ዘረፋ እንዳይፈጽምና ንብረት እንዳያወድም በመከላከል ኅብረተሰቡ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ አሳስበዋል።ምንጭ – ኢዜአ