EthiopiaLatestNews

የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አሰራሩን መቀየሩን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የሰነድ ማረጋገጫ ማህተም አሰራሩን መቀየሩን አስታወቀ። እየተበራከተ የመጣውን ሰነድ አስመስሎ የመስራት ወንጀል ለመቀነስ በማሰብ ኤጀንሲው ለሚሰጣቸው የልደት፣ የጋብቻ ፣ የፍቺ ፣ የያላገባ እንዲሁም የሌሎች ማስረጃዎች አገልግሎት ይጠቀምበት የነበረውን የማረጋገጫ አሰራር ወደ ዘመናዊነት በመቀየር አስመስሎ መስራት እያደረሰ ያለውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳት ለመቀነስ የበኩሉን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል።ተቋሙ በዋና መስሪያ ቤት የሚሰጠውን የፖስፖርት ፣ የቪዛና ለተለያዩ የውጭ እና የሃገር ውስጥ ሰነዶች የሚውሉ ማስረጃዎች የሚረጋገጥበትን የቀድሞ የማህተም አሰራር በመተው በውጭ ሃገር አሰርቶ ባስገባው ዘመናዊ የሆሎግራም ማረጋገጫ አሰራር ከዛሬ ህዳር 13 2014 ዓ.ም ጀምሮ በመተካት ተግባራዊ እንደሚያደረግ አስታውቋል፡፡ይህ አሰራር ከፖስፖርት እና ከውጭ ጉዞዎች ጋር ተያይዞ በየቦታው ተመሳስሎ በሚሰሩ ሰነዶች ለማለፍ የሚደረገውን የአጭበርባሪዎች እንቅስቃሴ ለመግታት እገዛ የሚያደርግ እንደሚሆን ታምኖበታል።