EthiopiaLatestNews

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ

መንግስት በጦርነቱ ሳቢያ የሚከሰተውን ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳት ለመቀነስ እየሰራሁ ነው አለ::ዛሬ ረፋዱ ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች እስካሁን 12 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኖ በጦርነቱ ሳቢያ የወደመውን ምርት ለማካካስ እየተሰራ መሆኑንና ከዚህ ውስጥም 3 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታሩ ተሰብስቧል ብሏል::በተመሳሳይ ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በሀገር ውስጥ ለመተካት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ብሎም ከመደበኛው የመስኖ ስራ በመለስ በጦርነቱ የወደመውን ምርት ለማካካስ ለመስኖ ልማት ትኩረት መሰጠቱን ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰላማዊት ካሳ በመግለጫቸው ጠቅሰዋል::ከዚህም ባሻገር ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የቀረጥ ነጻ እድል ወይም አጎዋ ተጠቃሚነት ልትታገድ መሆኑን ተከትሎ አህጉራዊ የገበያ እድሎችን ለመጠቀም መንግስት አዳዲስ ገበያዎችን እየፈለገ መሆኑ ተመላክቷል::በሌላ በኩል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በሰጠው በዚሁ መግለጫ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በመላው ዓለም በተለያዩ 25 ከተሞች በተካሄዱ ሰልፎች ላይ የኢትዮጵያን እውነት ዓለም እንዲያውቅ ተደርጓል ተብሏል::ከሰልፎቹ በመለስ ታዲያ በጦርነቱ ሳቢያ እየደረሰ ያለውን ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳት ለመቀነስ ዳያስፖራው ገንዘቡን በህጋዊ መልኩ እንዲልክ ተጠይቋል::

81812 SharesLikeCommentShare