EthiopiaNews

በአዳማ ከተማ ድምፅ ለመስጠት የተመዘገቡ 312 ሺህ 456 መራጮች ከማለዳ ጀምሮ ድምፅ መስጠታቸውን እንደቀጠሉ ናቸው።

በአዳማ ከተማ ድምፅ ለመስጠት የተመዘገቡ 312 ሺህ 456 መራጮች ከማለዳ ጀምሮ ድምፅ መስጠታቸውን እንደቀጠሉ ናቸው።

🔸የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ከ296 የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ የተወሰኑት ጋር በመዘዋወር የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን ተመልክቷል።

🔸በአዳማ ከተማና አካባቢው 7 የፓለቲካ ፓርቲዎች ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤትና ለኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩ ሲሆን ምርጫውም በ3 የምርጫ ክልሎች እንደሚካሄድ ነው የተነገረው።

🔸ኢቢኤስ በምርጫ ጣቢያዎቹ ባደረገው ምልከታ የምርጫ ጣቢያ አስፈፃሚዎች ያለምንም መጓደል የምርጫ ቁሳቁሶችን ተረክበው በስራ ላይ ስመሆናቸው ከኃላፊዎቹ ሰምቷል።

🔸በተጨማሪም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማን የመሳሰሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ምርጫውን የሚታዘቡ ወኪሎቻቸውን በምርጫ ጣቢያዎች መወከላቸውን ነግረውናል።

🔸በአጠቃላይ በመላው ኦሮሚያ ለክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩ እጩዎች ቁጥር 178 ሲሆን ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የሚወዳደሩት ደግሞ 537 መሆናቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ ያሳያል።

👉አቤል አበበ ከአዳማ ያደረሰን መረጃ ነው፡፡

#EBS #EBSTVNEWS #ELECTION_2018 #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv