በ11 ወራት ከ3.3 ቢሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተይዛዋል ተባለ።
በድሬድዋ የጉምሩክ ቅርንጫፉ በ11 ወራት በአጠቃላይ ከ3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር መዋሉን ጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል።
በድሬድዋ ቅርጫፉ የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጣና የጉምሩክ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የገለጸው ነጻ የንግድ ቀጠናው ሥራ ከጀመረበት ከጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ከቀረጥና ታክስ ገቢ መሰብሰቡን ገልጿል።
በቅርንጫፍ ባለፉት 11 ባለፉት 40 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 38 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ወይም 96 ነጥብ 4 በመቶ መሰብሰብ መቻሉን ጠቁሟል።
ባለፉት 11 ወራት ከ3 ቢሊዮን ብር ከገቢ እንዲሁም 313 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ከወጪ በአጠቃላይ 3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር መዋሉን የጉምሩክ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
