ከስደት ተመላሽ ዜጎች
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺ 612 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሰቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 229 ወንዶችና 383 ሴቶች ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 134 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው ተብሏል።
መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ70 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል ነው የተባለው።
ሚኒስቴሩ ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመተባበር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
በተጨማሪም መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት ወደ ተለያዩ ሀገራት ሄደው የሚመለሱ የፍልሰት ተጎጂዎችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋም የሚያስችሉ ተግባራትን በትብብር እየተከናወነ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
