ከ 35 ሺህ በላይ ዜጎች ተገቢውን ማስረጃ በማቅረብ ጊዜያዊ መታወቂያ መውሰድ መቀጠላቸውን የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ከ 35 ሺህ በላይ ዜጎች ተገቢውን ማስረጃ በማቅረብ ጊዜያዊ መታወቂያ መውሰድ መቀጠላቸውን የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ገለጸ፡፡የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ኮሚሽነር ፍሰሃ ጋረደው ለአዲስ ነገር እንዳሳወቁት በሀገሪቱ የተደቀነውን የደህንነት ስጋት ተከትሎ በወጣው የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሰረት በእጃቸው መታወቂያም ሆነ ማንኛውንም ከሱ የሚስተካከል ማስረጃ የሌላቸውን ግለሰቦች ማንነታቸውን በማጣራት ህጋዊ ለማድረግ የተጀመረው ስራ መቀጠሉን ጠቅሰው በዚህም ለጥፋት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋልና ይፈጸሙ የነበሩ ወንጀሎችን መቀነስ መቻሉን ገልጸዋል፡፡በሌላ በኩል የጦር መሳሪያ ምዝገባውን በተመለከተም እስካሁን በመዲናዋ ከ 95 በመቶ በላይ የሚሆኑት የጦር መሳሪያዎች መመዝገባቸውን የገለጹ ሲሆን ይህም በከተማዋ በቀጣይ የደህንነት ስጋት እንደማይኖር ያረጋገጠ ነው ብለዋል፡፡ዘገባው የትእግስት ብርሃኔ ነው፡፡ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።Telegram: https://t.me/ebstvworldwideFollow us on: https://linktr.ee/ebstelevision#ኢቢኤስ#EBS