የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኢትዮጵያ የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ አባል እንድትሆን የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኢትዮጵያ የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ አባል እንድትሆን የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አፅድቆ ለህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት መርቷል።
ምክር ቤቱ ይሄን ውሳኔ ያሳለፈው ዛሬ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ባሳለፈው ውሳኔ ነው።
ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክን በአባልነት መቀላቀሏ የልማት ፋይናንስ፣ የመሠረተ ልማት ድጋፍ እና ለማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋት አማራጭ የገንዘብ ምንጮችን ለማግኘት የሚያስችላትና ከደቡብ ደቡብ የፋይናንስ ሥርዓቶች ጋር የሚኖራትን ትስስር የሚያጠናክር ነው ብሏል።
ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ በብሪክስ አባል ሃገራት በፈረንጆቹ 2015 የተመሰረተ እና መቀመጫውን በቻይናዋ ሻንጋይ ያደረገ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። መረጃው ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
