የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና ለምክክሩ
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ዙሪያ ሀገር አቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራውን ከግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የጋራ የቴክኒክ ኮሚቴ በሀገራዊ የምክክር ጉባኤው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ሚና የሚያጠናክር ሀገር አቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ እቅድ ይፋ አድርጓል።
ከሀገራዊ የምክክር ጉባኤው አስቀድመው የሚከናወኑ ተግባራት፣ በምክክሩ ወቅት የሚተገበሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና እና ከጉባኤው መጠናቀቅ በኋላ ባሉ ጊዚያቶች የሚከናወኑ ተግባራትም በዝርዝር የስራ ዕቅዱ ተካተዋል ተብሏል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
