EthiopiaNews

የአውሮፓ ህብረት ስለምርጫው

🔸የአውሮፓ ህብረት እና መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉት የ25 ሀገራት ኤምባሲዎች ግንቦት 24 2018 ዓ.ም የተደረገውን 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ እንደሚቀበሉት አስታወቁ።

🔸ህብረቱ እና የ25 ሀገራት ኤምባሲዎች ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ ግንቦት 24 የተደረገው ምርጫ እንዲሳካ አስተዋፅኦ ላደረጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ ተወዳዳሪዎች እና የሲቪል ማህበረሰብ አባላትን አድንቀዋል።

🔸የአፍሪካ ህብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ)ታዛቢ ቡድኖች ሀገራዊ ምርጫው በመታዘብ ለነበራቸው ተሳትፎ እውቅና እንደሚሰጡ እና የታዛቢ ቡድኖቹን ሪፖርት እንደሚጠብቁ በጋራ መግለጫቸው አስታውቀዋል።

👉መረጃው በኢትዮጵያ ከሚገኘው የአፍሪካ ህብረት የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews