የአፍሪኤግዚም ባንክ በፈረንጆቹ 2025 አመት የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት 6.8 ቢሊየን ዶላር መድረሱን አስታወቀ።
የአፍሪኤግዚም ባንክ በፈረንጆቹ 2025 አመት የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ስድስት ነጥብ ስምንት ቢሊየን ዶላር መድረሱን አስታወቀ።
ባንኩ ይሄን ያለው አዲስ ባወጣው የአፍሪካ የ2026 አመት የንግድ ሪፖርቱ ላይ ነው።
በአውሮፓውያኑ 2025 አመት 6.8 ቢሊዮን ዶላር የደረሰው የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት የ3 ወራት የገቢ ዕቃዎች ወጪን መሸፈን እንደሚችል በሪፖርቱ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት በፈረንጆቹ 2023 አመት ከነበረበት 2 ቢሊየን ዶላር በ2025 ከሦስት እጥፍ በላይ ዕድገት ማስመዝገቡን የአፍሪ ኤግዚም ባንክ ሪፖርት ያሳያል። መረጃው ከአፍሪ ኤግዚም ባንክ ሪፖርት የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
