የኢትዮጵያና ቻይና ቋሚ ኮሚቴ አባላት
በአሁኑ ወቅት ቻይና በኢትዮጵያ ያላት ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ከ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሲደርስ ከ 2 ሺህ በላይ የቻይና ፕሮጀክቶች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑ ተገልጿል።
በዚሁም ከ560 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የሥራ እድል መፍጠር ማቻሉን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት 2 ቋሚ ኮሚቴዎች ከቻይና ብሄራዊ ሕዝባዊ ኮንግረስ የትምህርት፣ ሳይንስ፣ የባህልና የሕብረተሰብ ጤና ኮሚቴ ሊቀመንበር ሉኦ ሹጋንግ የተመራ የልዑክ ቡድንን ተቀብለው በተወያዩበት ወቅት ነው ይህ የተገለጸው።
በዚሁ ወቅት ቻይና ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ50 በላይ ለሚሆኑ ሀገራት ከቀረጥ ነጻ የገበያ እድል የሰጠች በመሆኑ የኢትዮጵያን ምርቶች በብዛት ወደ ቻይና በመላክ ሀገሪቱ ተጠቃሚ እንድትሆን መስራት ይገባል ተብሏል።
እንዲሁም ቻይና ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የሥራ እድል በመፍጠርና የእውቀትና ሽግግር በማድረግ በሰው ኃብት ልማት ዘርፍ ለሀገሪቱ ዕድገት የበኩሏን ሚና እየተወጣች ነው የተባለ ሲሆን ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች፣ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ለመንግሥት ሠራተኞች የምትሰጠውን ነጻ የትምህርት እድል አጠናክራ እንድትቀጥል ጥሪ ቀርቧል።
በቻይና ብሔራዊ ሕዝባዊ ኮንግረስ የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ባህል እና ሕብረተሰብ ጤና ኮሚቴ ሊቀመንበር ሉኦ ሹጋንግ በበኩላቸው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች እየተጠናከረ መምጣቱን ገልጸው በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝም፣ በትምህርት በባህልና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ትስስሩን ለማጠናከር እንደሚሠሩም ተናግረዋል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
