EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በግጭት ዐውድ ውስጥ በሚገኙ ክልሎች የማኅበረ ሥነ-ልቦና ሕክምና ፈላጊ ታካሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩና አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎች ቁጥር ውስን መሆኑ እንዲሁም በጤና ተቋማት የሚስተዋለው ከፍተኛ የበጀት ውስንነት አሳሳቢ ጉዳዮች መሆናቸውን ገለጸ፡፡

ኮሚሽኑ ይሄንን የገለጸው በአዲስ አበባ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያና በትግራይ ክልሎች በሚገኙ 13 ሆስፒታሎች ላይ የማኅበረ ሥነ-ልቦና ጉዳት ያለባቸው ሰዎች የጤና መብት ክትትል ግኝትና ምክረ ሐሳብ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተወያየበት ወቅት ነው፡፡

በክትትሉ የአእምሮ ሕክምና አገልግሎት በተለያዩ ሆስፒታሎች መጀመሩና በጤና መድኅን መካተቱ እንደ በጎ እርምጃ ቢጠቀስም፤ ከፍተኛ የመድኃኒት እጥረት መኖሩ፣ የባለሙያዎችና የቴክኖሎጂ እጥረት እንዲሁም የበጀት ውስንነት አሁንም አሳሳቢ ችግሮች መሆናቸው ተገልጿል።

በመድረኩም የሚመለከታቸው አካላት ለአገልግሎቱ ተደራሽነትና ጥራት ትኩረት እንዲሰጡም አሳስበዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv